ሃማስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ሰርጥ ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተላለፈውን ውሳኔ መቀበሉን አሳውቋል።

ሃማስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በጋዛ ሰርጥ ዘላቂ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የተላለፈውን ውሳኔ መቀበሉን አሳውቋል። “ሃማስ በጋዛ ሰርጥ ላይ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ፣ የጋዛ ሰርጥ ሙሉ በሙሉ ከወታደራዊ እንቅስቃሴ ነጻ እንዲሆን፣ የእስረኞች ልውውጥ እንዲደረግ፣ መልሶ ግንባታ ሥራዎች እንዲሰሩ፣ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መኖሪያ ቦታቸው እንዲመለሱ፣ በጋዛ ሰርጥ ላይ ምንም ዓይነት የስነ-ሕዝብ ለውጥም ሆነ የግዛቱ መቀነስ እንዳይኖር እና በችግር ውስጥ ላሉ ወገኖቻች አስፈላጊውን እርዳታ እንዲቀርብ” በተመለከተ ሃማስን መስማማቱን በመግለጫው ተናግሯል። በዛሬው ዕለት የፀጥታው ምክር ቤት በተደረገው ስብሰባ 14 ሀገራት የውሳኔ ሃሳቡን የደገፉ ሲሆን ሩሲያ ግን ድምፀ ተአቅቦ አድርጋለች። በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩስያ አምባሳደር ቫሲሊ ኔቤንዚያ እንደተናገሩት የጋዛን የተኩስ አቁም ሀሳብ በህዝብ ዘንድ በግልፅ የማይታወቅ የውሳኔ ሃሳብ የያዘ በመሆኑ ፣ የውሳኔን ሀሳቡን በተመለከተ ሩሲያ ብዙ ጥያቄዎች አሏት ብለዋል። "የአሜሪካን ረቂቅ የውሳኔ ሃሳብ በተመለከተ ብዙ ጥያቄዎች አሉን፤ ምንም እንኳን ይህ ምክር ቤት አንዳንድ ውሳኔዎችን ቢቀበልም፤ የውሣኔ ሃሳቡን የመጨረሻ ግብ ግን ከአሸማጋዮቹ በስተቀር የሚያውቅ የለም ሲሉ አምባሳደሩ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ፤ በፍልስጤም ጉዳይ ባደረገው ስብሰባ ወቅት ተናግረዋል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik