ኮንጎ ሪፐብሊክ የሩስያን ኢንቨስትመንቶች እንደምትሻ ገለፀች
የሀገሪቱ የፕላን፣ ስታቲስቲክስ እና ክልላዊ ውህደት ሚኒስትር ኢንግሪድ ኦልጋ ጊዝላይን ኢቡካ-ባባክስ እንደገለጹት፤ "ከሩስያ ጋር ያለው ትብብር በኮንጎ የልማት ሂደት ውስጥ የሩስያ ኩባንያዎችን የላቀ ተሳትፎ በማበረታታት ሊጠናከር ይገባል። የእኛ የ2022-2026 ብሔራዊ የልማት እቅድ የሩስያ የግል ዘርፍ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ በርካታ ፕሮጀክቶችን ያካትታል" ብለዋል።
በተጨማሪም፤ ብራዛቪል ሩስያ ለሀገሪቱ ተፈጥሮአዊ የካፒታል ልማት ስትራተጂ የምታደርገውን አስተዋጽኦ በደስታ እንደምትቀበል፤ ከ #SPIEF2024 ጎን ለጎን ለሩስያ ሚዲያ ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia