የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት መስከረም ወር ውስጥ ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት የመራጮች ስብሰባ እንዲደረግ አወጁ

የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት መስከረም ወር ውስጥ ከሚካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በፊት የመራጮች ስብሰባ እንዲደረግ አወጁ የአልጄሪያ ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ቴቡን ቅዳሜ እለት ፊርማቸውን ባኖሩበት አዋጅ፤ ጷግሜ 2 ከሚካሄደው ቀጣይ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሶስት ወር በፊት፤ የመራጮች ስብሰባ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል። ይኸው አዋጅ፤ ከሰኔ 5 እስከ 20 ለሚከናወነው የመራጮች ዝርዝር ክለሳ ስልጣን እንደሚሰጥም መግለጫው ገልጿል። በአልጄሪያ ሕገ መንግሥት መሠረት ቴቡን እ.አ.አ በታህሳስ ወር 2019 ከተመረጡ በኋላ፤ አምስት ዓመት ለሚቆየው የስልጣን ዘመን ለሁለተኛ እና ለመጨረሻ ጊዜ ሊወዳደሩ ይችላል። ሆኖም፤ ፕሬዝዳንቱ ለሁለተኛ የስልጣን ዘመን ለመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው እስካሁን በይፋ አልገለፁም። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik