የሰኔ 3 የቀትር ዋና ዋና የዓለም ጉዳዮች፡-
🟠 አዲሷ የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ዋና ፀሃፊ ቬሮኒካ ሙኒ ንዱቫ ከቀጣናው ሰላምና ፀጥታ በተጨማሪ ስራ ፈጠራን የሚያበረታታ ኢኮኖምያዊ ውህደት፣ ኢንተርፕርኒየርሺፕ እና የስራ እድል ፈጠራ ቅድሚያ የሚሰጡባቸው ጉዳዮች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡
🟠 የደቡብ አፍሪካ ፓርቲ ኤም.ኬ የብሔራዊ ምክር ቤት አባላት ቃለ መሃላ እንዳይፈጽሙ ለማስቆም ሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤቱን እንደሚጠይቅ አስታወቀ።
🟠 የሴኔጋል ጠቅላይ ሚኒስትር በጋዛ ሰርጥ ፍልስጤማውያን ላይ እየደረሰ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በማውገዝ ለፍልስጤም ህዝብ አጋርነትን ጠየቁ።
🟠 የዩክሬን ጦር በሩስያ ቤልጎሮድ ክልል በምትገኘው ሼቤኪኖ ከተማ አድርሶ ሶስት የአካባቢውን ነዋሪዎች እንዳቆሰለ የክልሉ አስተዳዳሪ ገልፀዋል፡፡
🟠 ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን መሪ ሆነው ለሌላ ተጨማሪ የስልጣን ዘመን እንደሚመረጡ እምነታቸውን ገለፁ። በቅድምያ የምርጫ ውጤቶች ፓርቲያቸው ከ720 መቀመጫ 186ቱን እንዳገኘ አረጋግጧል።
🟠 የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ብሔራዊ ምክር ቤቱን በትነው ምርጫ እንዲካሄድ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡
🟠 የአርሜኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቁ ተቃዋሚዎች ያለፈውን ምሽት የሬቫን በሚገኘው የፓርላማ ህንፃ ፊት ለፊት ድንኳን ሰርተው ማሳለፋቸው ታውቋል።
🟠 በክራይሚያ የውሃ እና ኢነርጂ አቅርቦት ላይ በተጣለው እገዳ ምክንያት የደረሰው ጉዳት ከ14 ትሪልየን ሩብል በላይ መሆኑን የክሪሚያ ፓርላማ ኃላፊ ቭላድሚር ኮንስታንቲኖቭ አስታወቁ።
🟠 የአውስትራሊያ ሳይንቲስቶች ካልተለመደ የኒውትሮን ኮከብ የመነጨ ነው ተብሎ የሚገመት ተደጋጋሚ ምልክት ጠፈር ላይ መለየታቸውን ገለፁ፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia