ሱዳን ከሩስያ ጋር ያላትን ግንኙነት በማጠናከር የሀገሪቱን ሁኔታ ለማረጋጋት ትጥራለች ሲሉ የሱዳን ፖለቲከኛ ተናገሩ
የሱዳን የሽግግር ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ማሊክ አጋር በ #SPIEF2024 በተካሄደው የሩስያ-አፍሪካ የንግድ ውይይት ሲናገሩ "ሁኔታዎችን ለማረጋጋት እና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ እንዲያስችለን ከሩስያ ጋር ግንኙነት ለመመስረት እና ለማጠናከር እየሞከርን ነው" ብለዋል።
ሩስያ፤ በሱዳን ኢኮኖሚ ልማት ውስጥ ለምታደርገው ተሳትፎ አድናቆታቸውን የገለፁት ምክትል ሊቀመንበሩ፤ ሁለቱ ሀገራት "በስልታዊ የወታደራዊ ችግሮች አፈታት፣ በጤና አጠባበቅ እና በትምህርት ዘርፍ በርካታ የትብብር ስምምነቶችን በመፈራረም የዳበረ ታሪክ እንዳላቸው" ገልፀዋል።
"ከጎረቤቶቻችን ጋር ያሉንን ዓለምአቀፋዊ ጉዳዮች መፍታትን ጨምሮ፤ ለሩስያ ምስጋና ይግባና፤ ለሀገራችን መረጋጋት እና የተረጋጋ ልማት ለማምጣት እንዲሁም ከማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና ሌሎች ሀገራት ጋር ግኑኝነታችንን ለማሳደግ ጥረት እያደረግን ነው። ሀገራችንን እየበታተነ ያለ ግጭት ቢኖርም እዚህ ሆነን ስለሀገራችን ሰላማዊ ልማት ከማቀድ አያግደንም" ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia