ልዩ ቃለመጠይቅ| በሴራሊዮን በቅርቡ የሚከፈተው የሩስያ ኤምባሲ በሁለቱ ሀገራት መካከል ቅርርብ እንደሚፈጥር፤ የሴራሊዮን የማዕድን እና የመሬት ሃብት ሚኒስትር ተናገሩ
የኤምባሲው መከፈት የቪዛ እና የቆንስላ አገልግሎቶችን ለማግኘት ወደ ጊኒ መጓዝን በማስቀረት፤ ሂደቶችን ያቀላል ሲሉ ሚኒስትሩ ጁሊየስ ማታታይ ከ #SPIEF2024 ጎን ለስፑትኒክ ገልፀዋል።
"የሩስያን ቋንቋ፣ የሩስያን ትምህርት የሚስተምሩ እንዲሁም ሩስያውያንም ሴራሊዮናውያንን መረዳት እንዲችሉ የሚያስችሉ ማዕከላት" እንደሚኖሩ ጠቁመዋል።
በኢምባሲው የሚበረታታው የጋራ መግባባት እና ለባህላዊ እና የንግድ እሴቶችን ክብር መስጠት፤ የንግድ ግንኙነቱ ወሳኝ ገጽታ መሆኑን ሚኒስትሩ አንስተዋል።
ኤምባሲው በ2024 መጨረሻ እንደሚከፈት እና ሴራሊዮን በጉጉት እየተጠባበቀችው እንደሆነ ጠቁመዋል።
"የኤምባሲው መከፈት ትልቅ ስኬት ነው ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ማታታይ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia