የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን በመቃወም በዋጋዱጉ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች፤ ዋጋዱጉ ከሚገኘው የተባበሩት መንግስታት ቢሮ አጥር ገቢ ውጪ ሰላማዊ ሰልፍ ትናንት አርብ አካሂደዋል።
የቡርኪናቤ እና የሩስያ ባንዲራን እያውለበለቡ፤ "ተመድ ይውረድ"፣ "አይ.ሲ.ሲ ይውረድ" የሚል ባነሮችን ይዘው እንደነበር፤ የስፑትኒክ ጋዜጠኛ ያነሳው ፎቶ ያሳያል።
ሰልፈኞቹ፤ ባለፈው ሳምንት ተመድ ያወጣውን፤ የቡርኪናፋሶ ጦር አካል የሆኑት የመከላከያ እና ደህንነት ሀይሎች እና ለትውልድ ሀገር ደጀን በጎ ፈቃደኞች፤ በሲቪልያኖች ላይ በደል ፈፅመዋል የሚል ሪፖርት ለመቃወም እንደወጡ ታውቋል።
የሰልፉ ጥሪ የተደረገው በብሔራዊ የነዋሪዎች ዘብ ማኅበራት ነው።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia