ብሔራዊ ገንዘቦችን መጠቀም “ትክክለኛ መንገድ ነው” ሲሉ የቡርኪናፋሶ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ኃላፊ ገለፁ።
"መገበያያ ገንዘቡ ላይ ቁጥጥር የሌለው ሀገር ሙሉ ሉዓላዊነቱን ሊጠይቅ አይችልም። ለልማት አስፈላጊ መሳሪያ ነው፣ ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ስትራቴጂካዊ መሳሪያ ነው፤" ሲሉ ከ #SPIEF2024 ጎን ከሰፑትኒክ ጋር ቃለ መጠይቅ ያካሄዱት ማሃማዲ ኩሱቤ ተናግረዋል።
ከዚህ አንፃር፤ የአፍሪካ ሀገራት በመገበያያቸው የንግድ ግብይት እንዲያደርጉ ቭላድሚር ፑቲን ካቀረቡት ጥሪ ጋር ሙሉ በሙሉ እንደሚስማሙ ገልፀዋል። በተለይም አሁን "ዶላርን በመጠቀም አንዳንድ ሀገራት ላይ የበላይነት እና ማእቀብ እንዲተላለፍ" እየተደረገ መሆኑ፤ የፑቲን ጥሪን የበለጠ ተገቢ እንደሚያደርገው ኃላፊው አስምረውበታል።
ሆኖም፤ የራስ መገበያያ ገንዘብ መኖሩ ብቻ በቂ አይደለም፤ ሲሉ ማሃማዲ ኩሱቤ አስጠንቅቀዋል።
"የገንዘብ ፖሊሲ እንዲሁ ከአካባቢው ሁኔታ እና ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ መሆን አለበት" ሲሉም አጠቃለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia