በ #SPIEF፤ ዲአርሲ የግብርና ፕሮጀክቶችን በገንዘብ የሚደግፉ አጋሮችን ትሻለች
ሴንትፒተርስበርግ እየተካሄደ በሚገኘው የ #SPIEF2024 ጉባኤ ከስፑትኒክ ጋር ቃለመጠይቅ ያደረጉት፤ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የወጣቶች ሚኒስትር አማካሪ፤ ኪንሻሳ "ዝቅ አድርገው የማይመለከቱን እና እንደ እኩል የሚያዩን እውነተኛ አጋሮችን ትፈልጋለች" ብለዋል።
ጆናታን ዴቪድ ምቦምቦ በ #SPIEF2024 መድረክ የኮንጎ ልዑክ ተሳትፎን አስፈላጊነት አስምረውበታል።
"በተወሰነ ደረጃ ሩስያ ውስጥ የዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዓይኖች እና ጆሮዎች አሉ ማለት ነው።"
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia