ሞስኮ “ለአፍሪካውያን እጅግ ማራኪ እና አስተማማኝ ስትራቴጂካዊ አጋር ነች" ሲሉ አንድ ናይጄሪያዊ ተንታኝ ሞገቱ
"ሩስያ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ላይ ለመውጣት ለሚሞክሩ እና ለገንዘብ እና ኢኮኖሚያዊ ሉዓላዊነታቸው ለሚታገሉ ተራማጅ የአፍሪካ ሀገራት አስፈላጊ አጋር ነች" ሲሉ በሰርጌ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝት ላይ አስተያየት የሰጡት ኢሶፉ ቡባካር ካዶ ማጋጊ ለስፑትኒክ ተናግረዋል።
"ጉዞው ኢኮኖሚያዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ እና ወታደራዊ ትብብርን በማጠናከር እየጨመረ ከመጣው የፀጥታ እጦት ጋር ተያይዞ ስጋቶችን እና ውጥረቶችን የሚያረጋጋና የሚያቀል ነው" ሲሉ አስምረዋል።
እንደ ገለልተኛ የፋይናንስ አማካሪው ገለፃ፤ አብዛኞቹ የአህጉሪቱ ሀገራት ዋና የእህል፣ የማዳበሪያ እና የተራቀቁ የጦር መሳሪያዎች አምራች ወደ ሆነችው ሩስያ ፊታቸውን እያዞሩ ነው።
ወታደራዊ ትብብሩ “አስደናቂ ውጤት እንዳስገኘ” ጠቅሰው የማሊ፣ቡርኪናፋሶ ፣ ማእከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ እና የኒጀር የመከላከያ ሀይሎች፤ ለሩስያ ወታደራዊ ድጋፍ ምስጋና ይግባና አመረጋጋትን ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተቆጣጠሩ ነው ብለዋል።
"የሩስያ ፌዴሬሽን አንዳንድ አዲስ-ቅኝ ገዢዎች እና አዲሶቹ-ኢምፔሪያሊስት ኃይሎች እንደሚያደርጉት ሀብት ለመዝረፍ አይደለም ወደ አፍሪካ የምትመጣው" ሲሉ ተንታኙ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia