"ብዝሃነታችን አንድነታችን ነው፤" የብሪክስ ሀገራት ብዝሃነትን የማስተናገድ ልምድ አላቸው፤ ሌሎች ባህሎችን ለመጫን እየሞከሩ አይደለ፤ ሲሉ አንድ ኤክስፐርት ለስፑትኒክ ተናገሩ

"ብዝሃነታችን አንድነታችን ነው፤" የብሪክስ ሀገራት ብዝሃነትን የማስተናገድ ልምድ አላቸው፤ ሌሎች ባህሎችን ለመጫን እየሞከሩ አይደለ፤ ሲሉ አንድ ኤክስፐርት ለስፑትኒክ ተናገሩ "በባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ውስጥ አንድ ባሕል በሌሎች ላይ የበላይ መሆን አይችልም። [...] እኛ [የብሪክስ ሀገራት] ሌሎች ሀገራት እንደ ሌሎች የብሪክስ ሀገራት እንዲሆኑ ተጽዕኖ ለማድረግ እየሞከርን አይደለም። ታሪክህን እንቀበላለን፣ ብዝሃነትህን እንቀበላለን፤ ነገር ግን በብዝሃነታችን አንድ ነን እንላለን፤" ሲሉ የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ምክክር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፊላኒ ምተምቡ ተናግረዋል። ከብሪክስ በተቃራኒ፤ "ከተለያዩ ባህሎች የመጡ ሰዎችን እነርሱን እንዲመስሉ ለማድረግ የሚሞክሩት ምዕራባውያን ሀገራት፤ "ከብዝሃነት ጋር ትንቅንቅ ላይ ናቸው" ሲሉ ከ #SPIEF2024 ጎን በሰጡት ቃለ መጠይቅ ገልፀዋል። "በምዕራቡ ዓለም ውስጥም እንዲህ አይነት አካሄዶች ዘላቂ እንዳልሆኑ የተገነዘቡ ሌሎች ትውልዶች መጥተዋል። ሆኖም ይህን አመለካከታቸውን፤ የተለመደው የምእራቡ ዓለም የፖለቲካ አስተሳሰብ ውስጥ ማካተት አልቻሉም" ሲሉ ምቴምቡ አክለዋል። ኤክስፐርቱ በተጨማሪም ብሪክስ "ፀረ-ምዕራባውያን ድርጅት ነኝ ብሎ አያውቅም" ብለዋል። ባለሙያው እንደሚሉት፤ “የምዕራባውያን ሀገራት የባለ ብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓትን እንደ ሥጋት ሊመለከቱ አይገባም።" የብሪክስ የባለሙያዎች ፎረም "ብሪክስ አዲስ የዓለም ስርዓት ፍለጋ ላይ ያለው ሚና" በሚል መሪ ቃል፤ ትናንት ሐሙስ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም #SPIEF2024 ተካሂዷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik