የሩስያ ባለሀብቶች የዚምባብዌን በርካታ የኢንቨስትመንት እድሎች እንዲቃኙ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ ጋበዙ
ዚምባብዌ የገጠሟት ፈተናዎች በዓለምአቀፍ ደረጃ የጋራ እርምጃ ያስፈልጋቸዋል። ይህ ማንም ወደኋላ የማይቀርበት የሰላም እና ልማት ትልም ማጠናከር እንዳለብን ሊያስገነዝብ ይገባል፤ ሲሉ የዚምባቡዌ ፕሬዝዳንት ኢመርሰን ምናንጋግዋ በ #SPIEF2024 ምልአተ ጉባኤ ላይ ተናግረዋል።
"ዚምባብዌ ለንግድ ክፍት ነች፤ ዚምባብዌ በሁሉም የኢኮኖሚ ዘርፎች ኢንቨስትመንትን፣ አጋርነትን እና ትብብርን በደስታ ትቀበላለች።"
በተጨማሪም ሩስያን "የዓለም አጋር" በማለት ገልፀዋታል። የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት፤ ሩስያ በማዳበሪያ አቅርቦት ላደረገችው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia