የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛውን፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዓመታዊ በጀት አፀደቀ

የኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛውን፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ ዓመታዊ በጀት አፀደቀ የሚንስትሮች ምክር ቤት፤ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ፤ ለቀጣዩ የ2017 በጀት ዓመት፤ 1 ትሪሊዮን ብር የሚጠጋ በጀት አጽድቆ፤ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መምራቱን አስታውቋል። የ2017 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት፤ የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል በሆነው የ2016-2018 የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ስር የተቀመጡ ግቦችን እና፤ የ2017-2021 የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍን ማስፈጸም እንዲቻል ተድርጎ መዘጋጀቱን ምክር ቤቱ ጠቅሷል። ምክር ቤቱ በዛሬው እለት ያፀደቀው በጀት፤ "ለፌዴራል መንግስት መደበኛ ወጪዎች፣ ለካፒታል ወጪዎች፣ ለክልሎች ድጋፍ፣ ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ እና ለተጠባባቂ ወጪ እንደሚውል" የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መግለጫ አመላክቷል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik