ደቡብ አፍሪካ ከሩሲያ አልማዝ አምራቾች ጋር መሥራት እንደምትፈልግ የደቡብ አፍሪካ አልማዝ ንግድ ዋና ስራ አስፈፃሚ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ#SPIEF2024 ወቅት ተናገሩ
ኖሲፊዎ ምዛሞ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት የሩሲያ አልማዝ ላይ የተጣለው እገዳ እንደሚነሳ ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፤ ደቡብ አፍሪካ የሩስያ አልማዝን እሴት ጨምራ ለዓለም ገበያ ማቅረብ እንደምትችል ገልጸዋል።
90 በመቶ የሚሆነውን የአለማችንን የአልማዝ ምርት የሚሸፍኑት አፍሪካ እና ሩሲያ ከመሆናቸው አንጻር ፤ምዕራባውያን በሩሲያ የተመረቱት አልማዞች ላይ በጣሉት ማዕቀብ ሳቢያ "ትልቅ" የአልማዝ አቅርቦት እጥረት መኖሩንምዛሞ ጨምረው ገልጸዋል።
ዋና ሥራ አስፈፃሚው እንዳሉት "ነገሮች በፖለቲካዊ መንገድ እንዲፈቱ እና ያሉ ጉዳዮች መፍትሄ እንደሚያገኙ እምናለሁ ፤ከዚያም የሩሲያ አልማዞች እንደገና ወደ ዓለም ገበያው እንደሚቀላቀሉ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia