ሴራሊዮን ለአልማዝ ንግዷ፤ በብሪክስ ገበያ እድል ማግኘት እንደምትችል የሪፐብሊኩ የማዕድን ሀብት ሚኒስትር ጁሊየስ ማታታይ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ #SPIEF2024 ላይ ተናግረዋል
"ለብሪክስ ሀገራት በተለይም በባህላዊ የአልማዝ ማዕድን ማውጣት ሂደትን እንዲያዘምኑልን እድል መሥጠት እንፈልጋለን። ይህ የኢንቨስትመንት ድጋፍ ለማግኘት እድል ይሰጠናል፤ ብሪክስ እንዲህ ያለውን እድል እንደሚሰጠን ሙሉ እምነት አለኝ። ሲሉ "በአልማዝ ኢንዱስትሪ የብሪክስ ትብብር ልማት" ዘርፍ ጉባኤው ላይ ተናግሯል።
የዚምባብዌ ማዕድንና ልማት ሚኒስትር ዊንስተን ቺታንዶም፤ ብሪክስ "በአልማዝ ገበያ ልማት ውስጥ ትልቅ ሚና ሊጫወት የሚችል ስብስብ እንደሆነ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia