የግንቦት 29 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
🟠 ፑቲን ከሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ፎረም #SPIEF2024 ጉባኤ ተሳታፊ እንግዶች ጋር፤ ተከታታይ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችን ማድረግ ጀምረዋል። ፑቲን ከቦሊቪያው መሪ ጋርም ተወያይተዋል።
🟠 ዩክሬን የዛፖሮዚያ የኒውክሌር ማመንጫን ስለ መምታቷ ማስረጃ አለ፤ ሁሉም የደረሱ ጉዳቶች፣ ሞት እና ውድመት፤ በምርመራው ተመዝግበዋል፣ ሲሉ የዛፖሮዚይ ክልል ገዥ ይቪግኒ ባሊተሰኪ በሴንትፒተርስበርግ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ጉባኤ #SPIEF2024 ላይ ተናግረዋል።
🟠 የዩክሬን ጦር ሃይል የሉጋንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክን (LPR) እንዲሁም የሉጋንስክ እና የክራስኖዶን ከተሞችን ጨምሮ በምዕራባውያን የረዥም ርቀት የጦር መሳሪያዎች በተደጋጋሚ መምታት መጀመሩን የሉጋንስክ ህዝቦች ሪፐብሊክን ኃላፊ ሊዮኒድ ፓሴችኒክ ተናገረዋል።
🟠 አሜሪካ ለዩክሬን ጦር ሞስኮ እና ክሬ ምሊንን፤ በአሜሪካ ጦር መሳሪያዎች እንዲመቱ ፈቃድ የመስጠት ፍላጐት እንደሌላት ባይደን ተናግሯል።
🟠 የኔቶ ኃላፊ ስቶልተንበርግ እንዳሉት ከሩሲያ በኩል ምንም አይነት ፈጣን ወታደራዊ ስጋት የለም፤ኔቶም ወታደሮችን ወደ ዪክሬን የመላክ እቅድ የለውም ሲሉ አፅንኦት ሰጥተው ተናግዋል።
🟠 ስፔስ ኤክስ የፕሮቶታይፕ መንኮራኩር ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳካ ሁኔታ ማረፏን ዘግቧል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia