ሩሲያ ከበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ጋር ቪዛን ማስቀረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እየተወያየች ነው።
የሩሲያ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የፕሬስ አገልግሎት በዛሬው እለት፤የአፍሪካ ሀገራትን በስም ሳይጠቅስ ፤ ቪዛን ማስቀረት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከተወሰኑ የአፍሪካ ሀገራት ጋር እየተወዩ መሆናቸውን ተናግዋል።
እ.አ.አ በነሐሴ 2023 ሩሲያ ከቻይና እና ኢራን ጋር ያለ ቪዛ የቡድን ጉብኝት መፍቃዷ ይታወሳል። እ.ኤ.አ. በ 2024 በሩሲያ እና በህንድ መካከል ተመሳሳይ የቡድን ቪዛ-ነጻ የጉብኝት ልውውጥ ለመጀመር እቅደዋል።
እ.አ.አ በ2023 ሩሲያ ለኩዌት፣ ለሳዑዲ አረቢያ፣ ለባህሬን፣ ለኦማን እና ለማሌዢያ ዜጎች፤ የቱሪስት ቪዛዎችን ሙሉ በሙሉ ማስቅረቱን ሚኒስቴሩ አስታውቋል። በ2024 በተመሣሣይ መልኩ ሊቀጥል ይችላል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia