በደቡብ አፍሪካ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በትንሹ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ
በደቡብ አፍሪካ ምስራቃዊ የባህር ጠረፍ ባለስልጣናት እንዳሉት ፤በከባድ ዝናብ ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ ቢያንስ 18 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቀዋል።
በጎርፉ ክፉኛ የተጎዳው የኔልሰን ማንዴላ ቤይ ማዘጋጃ ቤት ቃል አቀባይ ለኤኤፍፒ እንደገለጹት፤በምስራቃዊ ኬፕ ግዛት ቢያንስ ሰባት ሰዎች መሞታቸው ተናግረዋል። በተጨማሪም፣ የኩዋዙሉ-ናታል ግዛት፣ አጎራባች ግዛት፣ ቢያንስ 11 ሰዎች በወደብ ከተማዋ ደርባን እንዲሁም በዙሪያው ካሉ አካባቢዎች፣ መሞታቸውን ዘግቧል።
ከኔልሰን ማንዴላ ቤይ ከ2,000 በላይ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፤ብዙዎቹም ቤቶች ለመኖሪያ ምቹ ያለሆኑ መሆናቸው ተገልጿል።
የምስራቃዊ ህንድ ውቅያኖስ የባህር ዳርቻ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ አጋጥሟቸዋል፤ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙት ዘጠኝ አውራጃዎች መካከል ፤ አራቱ የአየር ሁኔታ ማስጠንቀቂያ ከሜትሮሎጂ አገልግሎት እንደደረሳቸው ተገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia