የግንቦት 26 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች

የግንቦት 26 ምሽት ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች 🟠 የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ በጊኒ ሪፐብሊክን ጉብኝታቸው ወቅት ከጊኒ አቻቸው ሞሪሳንዳ ኩያቴ ጋር ተወያይተዋል። 🟠 ክላውዲያ ሺንባም የሜክሲኮ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫን በማሸነፋቸው ቭላድሚር ፑቲን የእንኳን ደስ ያሎት መልእክታቸውን ማስተላለፋቸውን ክሬምሊን አስታውቋል። 🟠 የሩስያ ፌዴራል የጸጥታ አገልግሎት ፤ በሩሲያ መሰረተ ልማቶች እና በወታደራዊ መኮንኖች ላይ በማሴር ጉዳት ለማድረስ በሴባስቶፖል ግዛት ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የዩክሬን የስለላ ወኪሎች መረብ ማግኘቱን ኤጀንሲው አስታውቋል። 🟠 ኔታንያሁ ታጋቾችን ለማስለቀቅ በጋዛ የሚካሄደውን ወታደራዊ እርምጃ ለ42 ቀናት ለማቆም ፍቃደኛ መሆናቸውን አስታውቀዋል፤ ነገርግን ሁሉም አላማዎች እስኪሳኩ ድረስ ጦርነቱን ማቆም እንደማይችሉ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። 🟠 የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት መሀመድ ሞክበር በመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በእጩነት አይመዘገቡም። 🟠 የሩስያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት በኖርድ ስትሪም የነዳጅ ማስተላለፊያ ላይ የተፈፀመውን የአሸባሪዎች ጥቃት አስመልክቶ ለአሜሪካ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ቆጵሮስ ተጨማሪ ጥያቄዎችን ልኳል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik