ሩሲያ እና ጊኒ 65 አመታትን በወዳጅነት እና በትብብር የዘለቀ ግንኙነት
የሩስያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ በትላንትናው እለት ለሥራጉብኝት ጊኒ የገቡ ሲሆን፥ የሁለትዮሽ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ ግንኙነት በተመለከተ አንዳንድ እውነታዎች
🟫 ላቭሮቭ ለመጨረሻ ጊዜ ጊኒን የጎበኙት እ.አ.አ በ2013 ነበር።
🟫 የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሁን አፍሪካ ጉብኝት ባለፉት ሁለት አመታት ጊዜ ወዲህ ለስድስተኛው ጊዜ የተደረገ ነው። ሚኒስትሩ ባለፈው ነሀሴ ወር በደቡብ አፍሪካ በተደረገው የብሪክስ ስብሰባ ተከፈለው ነበር።
🟫 ሩሲያ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2 ቀን 1958 ለጊኒ ነፃነት እውቅና የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ነበረች ። በሁለቱ መንግስታት መካከል ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረውም፤ ነጻነቱን ካወጀች ከሁለት ቀናት በኋላ ነበር።
🟫 የሁለቱ ሀገራት መካከል እያደገ የመጣ ፤የንግድ፣ የኢኮኖሚ እና የትምህርት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ያሉ ትብብሮች አሉ።
🟫 የምዕራብ አፍሪካ ሀገር ጊኒ በሞስኮ በሚያዘጋጁ፤ የባለብዙ ወገን ስብሰባዎች ላይ በየጊዜው ትሳተፋለች። ለምሳሌ እ.ኤ.አ. በ2023 በተካሄደው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ የአገሪቱ ተወካዮች ተሳትፈዋል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia