ሳውዲ አረቢያ በስዊዘርላንድ በሚካሄደው የዩክሬን የሰላም ስብሰባ ላይ እንደማትገኝ ዘገባዎች አመላክተዋል።

ሳውዲ አረቢያ በስዊዘርላንድ በሚካሄደው የዩክሬን የሰላም ስብሰባ ላይ እንደማትገኝ ዘገባዎች አመላክተዋል። ሀገሪቱ ውሳኔውን ያስተላለፈችው፤ሩሲያ በስብሰባው ላይ የማትወከል በመሆኗ ነው ሲል የጀርመን የዜና ወኪል ዲፒኤ እሁድ እለት የሳዑዲ የዲፕሎማቲክ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል። የዩክሬኑ ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ በሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ቅዳሜ ሊደረግ ያሰበው ጉብኝት ፣የታቀደው ከሰላም ስብሰባ በኋላ ሊሆን እንደሚችል ዘገባው አስነብቧል። ሳዑዲ አረቢያ በጉባኤው ላይ ላለመሳተፍ መወሰኗን እስካሁን በይፋ አላሳወቀችም። ስዊዘርላንድ ከሰኔ 15-16 በዩክሬን ግጭት ዙሪያ የሚካሄድ የሰላም ስብሰባን ታስተናግዳለች። በሚያዝያ ወር በበርን የሚገኘው የሩሲያ ኤምባሲ ቃል አቀባይ ቭላድሚር ክሆክሎቭ ለስፑትኒክ እንደተናገሩት ስዊዘርላንድ ሩሲያን ወደ በጉባኤው እንድትካፈል እንዳልጋበዘቻች በመግለጽ ፤ ሞስኮ ብትጋበዝ እንኳን በዝግጅቱ ላይ የመሳተፍ እቅድ እንደሌላት ተናግሯል። ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
Sputnik