የግንቦት 26 ረፋድ ዋና ዋና የዓለም ዜናዎች
🟠 የሩስያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን በጊኒ ጀምረዋል።
🟠 በቅርቡ በተካሄደው የፓርላማ ምርጫ ገዥው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ ከ70 በላይ መቀመጫዎችን ማጣቱን ተከትሎ፤ የደቡብ አፍሪካ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሀገሪቱ ጥቅም እንዲሰሩ ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጥሪ አቅርበዋል።
🟠 የሶማሊያ ፕሬዝዳንት የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ሁሴን ሞአሊም ፤ የሶማሊያ መንግስት እ.ኤ.አ. በ2024 መጨረሻ ላይ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን ከሶማሊያ እንድታስወጣ መጠየቃቸውን ተናግረዋል።
🟠 የናሚቢያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከጥር 2025 ጀምሮ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፤ ዝቅተኛ የደመወዝ መነሻ ክፍያን ለመተግበር ፣የሰራተኛ የኢንዱስትሪ ግንኙነት እና የስራ እድል ፈጠራ ሚኒስትር ውሳኔውን ማፅደቃቸውን ተናግረዋል።
🟠 ዩክሬን በኬርሰን ከተማ በሰላማዊ ሰዎች ላይ ድንገተኛ ግድያ በተቀነበበረ መልኩ ለመፈጸም ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ፤በከተማው ውስጥ የሚገኙ የሩስያ ደጋፊ የምስጢር ቡድን ተወካዮች ለሪያ ኖቮስቲ ተናግረዋል ።
🟠 ግብፅ ከሩሲያ ጋር በራሳቸው ገንዘብ ልውውጥ ለማድረግ እየተወያየች ነው ሲሉ የሀገሪቱ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አስታውቀዋል።
🟠 የገዢው ፓርቲ እጩ ክላውዲያ ሺንባም ከ58.3% እስከ 60.7% ድምጽ በማግኘት የሜክሲኮ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫዎችን ማሸነፋቸውተነግሯል። የወቅቱ ፕሬዝደንት፤ ሼይንባን እንኳን ደስ አለዎት! የሚል መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
🟠 ትራምፕ በጁላይ 11 በኒውዮርክ ከሚጠበቀው የፍርድ ቤት ውሳኔ ምንም ይሁን ምን ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት በእጩነት ይቀርባሉ፤ ሲሉ የሪፐብሊካን ብሄራዊ ምርጫ ኮሚቴ ሰብሳቢ ላራ ትራምፕ ለምዕራቡ አለም መገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል ።
🟠 ሩሲያ ውስጥ ሰው በሰራሽ አስተውሎ ዘዴ ፤ የተጠቀለሉ ፅሁፎች ሳይገለጡ ለማንበብ እንዲቻል ተደርጓል። የወረቀት ወይም የበርች ቅርፊት ጥቅል ፤እንዲሁም መጻሕፍትን በሲቲ ስካን ማሽን ውስጥ በማስገባት፤ የዲጂታል ቅጂ እንዲሰጥ ተደርጓል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia