ሩስያ በተያዘው የግብርና ዓመት እስከ 70 ሚልየን ቶን እህል፤ 53 ሚልየን ቶን የስንዴ እህልን ጨምሮ፤ ወደ ውጭ እንደምትልክ የሩስያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተናገሩ።
ባለፈው ዓመት መገባደጃ፤ የሩስያ ገበሬዎች ወደ 150 ሚልየን ቶን እህል መሰብሰባቸውን፤ ዲሚትሪ ፓትሩሼቭ ተናግረዋል። አክለውም ሩስያ 12% የስንዴ እና 14% የዓለም የገብስ ምርት ድርሻን በመያዝ፤ ከዓለም ግንባር ቀደም እህል አምራቾች አንዷ መሆኗን በድጋሚ አረጋግጣለች ብለዋል።
እንደ እርሳቸው ገለጻ፣ እንዲህ ዓይነቱ መነሻ ሩስያ የራሷን የምግብ ዋስትና መለኪያዎች እንድታሟላ እና ወደ ውጭ የምትልካቸውን ምርቶች እንድታሳድግ ያስችላታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia