ሩሲያ እና ታንዛኒያ ዕምቅ የማዕድን ሀብቶችን ለማውጣት የሥነ-ምድር ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

© telegram sputnik_ethiopiaሩሲያ እና ታንዛኒያ ዕምቅ የማዕድን ሀብቶችን ለማውጣት የሥነ-ምድር ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ
ሩሲያ እና ታንዛኒያ ዕምቅ የማዕድን ሀብቶችን ለማውጣት የሥነ-ምድር ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ - Sputnik አፍሪካ, 1920, 09.06.2026
ሰብስክራይብ

ሩሲያ እና ታንዛኒያ ዕምቅ የማዕድን ሀብቶችን ለማውጣት የሥነ-ምድር ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

​ በሥነ-ምድር እና ከመሬት በታች ሀብቶች አጠቃቀም ረገድ፤ በሩሲያ እና በታንዛኒያ መካከል ጠንካራ የትብብር አቅም እንዳለ፤ የሩሲያ የተፈጥሮ ሀብት እና አካባቢ ጥበቃ ምክትል ሚኒስትር ዲሚትሪ ቴቴንኪን የሁለቱ ሀገራት ተወካዮች ካደረጉት ስብሰባ በኋላ ተናግረዋል።

​ የታንዛኒያ የማዕድን ሀብት — ወርቅ፣ ኮባልት፣ ኒኬል፣ መዳብ፣ ቆርቆሮ፣ አልማዝ እና ሃይድሮካርቦኖች — በሚገባ አልተጠኑም ሲሉ የታንዛኒያ የማዕድን ሚኒስትር አንቶኒ ማቩንዴ ግልጽ አድርገዋል።

ሚኒስትሩ፤ "ሩሲያ በሥነ-ምድር አሰሳ ረገድ ሰፊ ልምድ አላት። ሀገርዎን በዚህ ዘርፍ እንደ መሪ አጋር እንመለከታታለን" ማለታቸውን የሩሲያ የተፈጥሮ ሀብት እና አካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር ገልጿል።

​ሁለቱ አካላት መረጃ ለመለዋወጥ እና ቀጣይ የትብብር እርምጃዎችን ለማሠናዳት ተስማምተዋል።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0