ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የውጭ ኢንቨስተሮች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደላቸው
08:02 09.06.2026 (የተሻሻለ: 08:04 09.06.2026)

© telegram sputnik_ethiopia
ሰብስክራይብ
ኤምባሲዎች፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና የውጭ ኢንቨስተሮች በራሳቸው የውጭ ምንዛሬ ነዳጅ እንዲያስገቡ ተፈቀደላቸው
በአዲሱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ መሠረት እነዚህ አካላት ከዚህ በኋላ ከሀገር ውስጥ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መጠየቅ ሳይጠበቅባቸው በፍራንኮ ቫሉታ ስርዓት ነዳጅ ገዝተው ማስገባት ይችላሉ።
ሆኖም በዚህ አዲስ አሠራር ላይ ገደቦችም ተቀምጠዋል፦
የሚመለከተው ለተቋማቱ ፍጆታ የሚውል ነዳጅን ብቻ ነው፣
ለንግድ ዓላማ ነዳጁን መልሶ መሸጥ የተከለከለ ነው፣
የነዳጅ ግዢ እና ሥርጭቱ ጥብቅ የመንግሥት ቁጥጥር ይደረግበታል።
መመሪያው የውጭ ምንዛሬ እና የነዳጅ አጠቃቀምን ሥርዓት ለማስያዝ ያለመ እንደሆነ ተነግሯል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X