ሦስት የአፍሪካ አገራት የኢቦላ ወረርሽኝን ለመግታት ድንበር ተሻጋሪ ትብብር እንዲጠናከር ጠየቁ

ሰብስክራይብ

ሦስት የአፍሪካ አገራት የኢቦላ ወረርሽኝን ለመግታት ድንበር ተሻጋሪ ትብብር እንዲጠናከር ጠየቁ

የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ፣ ኡጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ከቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጤና ድርጅቶች ጋር በመሆን ወረርሽኙን ለማስቆም፣ ማኅበረሰቦችን ለመጠበቅ እና በአኅጉሪቱ ጠንካራ የጤና ሥርዓት መኖሩን ለማረጋገጥ በተወሰኑ እርምጃዎች ላይ ለመስማማት መድረሳቸውን በጋራ በወጣው መግለጫ ላይ ተመልክቷል።

ከተቀመጡት የድርጊት መርሃ-ግብሮች መካከል ጥቂቶቹ፦

የጋራ ክትትልን፣ የእውነተኛ ጊዜ የመረጃ ልውውጥን እና የታካሚ ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመከታተል ሥራን ማጠናከር፤

በድንበር መግቢያ ኬላዎች ላይ የጤና ምርመራዎችን ማቀናጀት እና የሕዝብን እንቅስቃሴ መከታተል፤

የጤና ባለሙያዎችን እና ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ የድንበር አካባቢ ማኅበረሰቦችን መጠበቅ፤

ፈጣን ምርመራ ለማድረግ እና የናሙና ትራንስፖርትን ለማሳለጥ የላቦራቶሪ አቅምን ማሳደግ፤

ለፈጣን ምላሽ የሚረዱ ሠራተኞችን ማሠልጠን እና የሕክምና ቁሳቁሶችን አስቀድሞ ማዘጋጀት፤

ከአጋር አካላት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እና የሥራ ማስኬጃ እገዛን ማሰባሰብ።

በእንግሊዘኛ ያንብቡ

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0