ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከመጪው ታኅሣሥ 3 እስከ 6 እንደሚካሄድ ተገለፀ
11:30 09.12.2025 (የተሻሻለ: 11:44 09.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሀገር አቀፍ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከመጪው ታኅሣሥ 3 እስከ 6 እንደሚካሄድ ተገለፀ
የክትባት ዘመቻው ከ25 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን ተደራሽ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።
ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ሕፃናት የቤት ለቤት የፖሊዮ ክትባት የሚሰጥ ሲሆን የበሽታው ምልክት ያሳዩትን ሕፃናት የመለየት ሥራ ይከናወናል ተብሏል።
ለአራት ቀናት ለሚቆየው ዘመቻ የክትባት ቁሳቁስ እና ተያያዥ የግብዓት አቅርቦትን ጨምሮ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅቶች በሁሉም ክልሎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ መገለፁን የሀገር ውስጥ ሚዲያ ዘግቧል።
ሀገሪቱ በቅርቡ በ7 ክልሎች ውስጥ በሚገኙ 22 ዞኖች ባካሄደችው ዘመቻ፤ ከአምስት ዓመት በታች እና ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትን ጨምሮ ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የፖሊዮ ክትባት እንዲያገኙ አድርጋለች፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X