የሳኅል ሀገራት ጥምረት የናይጄሪያ ጦር አውሮፕላን አየር ክልሌን ጥሷል ሲል ከሰሰ
10:36 09.12.2025 (የተሻሻለ: 10:44 09.12.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሳኅል ሀገራት ጥምረት የናይጄሪያ ጦር አውሮፕላን አየር ክልሌን ጥሷል ሲል ከሰሰ
የኮንፌዴሬሽኑ መግለጫ እንዳመለከተው፤ ፈቃድ የሌለው ሲ-130 አውሮፕላን ሰኞ ዕለት በቡርኪና ፋሶ ቦቦ-ዲዩላሶ ላይ እንዲያርፍ ተደርጓል።
በአውሮፕላኑ ውስጥ ሁለት የበረራ ሠራተኞች እና ዘጠኝ መንገደኞች የነበሩ ሲሆን ሁሉም ወታደራዊ አባላት እንደሆኑ ታውቋል።
የሳኅል ሀገራት ጥምረት ክስተቱ የአየር ክልሉን እና የአባል ሀገራቱን ሉዓላዊነት እንደጣሰ በመጥቀስ በፅኑ አውግዞታል።
ደህንነትን ለማረጋገጥ "የሳኅል ሀገራት ጥምረት የአየር ክልልን የሚጥስ ማንኛውም አውሮፕላን ላይ እርምጃ ለመውሰድ" ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
በክስተቱ ዙሪያ ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል።
በሰው ሠራሽ አስተውህሎት የበለጸገ ምሥል
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X