የባማኮ 2025 የመከላከያ ዘርፍ አውደ ርዕይ ሀገር በቀል ተሰጥኦ ማሳያ እና ማሊ ለንግድ ክፍት መሆኗን ማረጋገጫ ነው - ኃላፊዎች
11:48 14.11.2025 (የተሻሻለ: 11:54 14.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የባማኮ 2025 የመከላከያ ዘርፍ አውደ ርዕይ ሀገር በቀል ተሰጥኦ ማሳያ እና ማሊ ለንግድ ክፍት መሆኗን ማረጋገጫ ነው - ኃላፊዎች
ተሳታፊዎች ለሀገር ውስጥ ፈጠራ እና ለዓለም አቀፍ ትብብር ወሳኝ ሚና ያለው መድረክ አድርገው የገለፁት የባማኮ 2025 የመከላከያ አውደ ርዕይ ሶስተኛ ቀኑ ላይ ደርሷል፡፡
ሁነቱ ወጣት መሃንዲሶች ሥራዎቻቸውን በይፋ ማሳየት እንዲችሉ እና ድጋፍ እንዲያገኙ አቅም ሆኖ ያገለግላል ሲሉ ከማርካላ ማዕከላዊ ወታደራዊ ወርክሾፕ የመጡት ኮሎኔል ሞሀመድ ሰይባ ሲስኮ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
የማሊ የጦር መሳሪያ ጥይት አምራች የሆነው ካርማ አውደ ርዕዩን ለአዳዲስ አፍሪካዊ ትብብሮች በር ከፋች ሲል ገልጾታል፡፡
“ይህ ሁነት በ25 ዓመታት ውስጥ የመጀምሪያው ነው፡፡ እኛ ብዙውን ግዜ በጀርመንም፣ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ በሚዘጋጁ ዓለም አቀፍ አውደ ርዕዮች ላይ ነው የምንሳተፈው፡፡ ነገር ግን በማሊ ይህ ለመጀመሪያ ግዜ ነው” ሲሉ ኦፕሬሽን ዳይሬክተሩ አሊዮ ሰይላ ለሰፑትኒክ ሀሳባቸውን አጋርተዋል፡፡
አውደ ርዕዩ የማሊን መረጋጋት እና ግልጽነት አሳይቷል ያሉት ደግሞ የማሊ የሴቶች አብሮነት እና ነጻነት ፕሬዝዳንት አይቼ ባባ ኬይታ ናቸው።
“ጥቂቶች ባማኮ ወድቃለች ብለው ቢያስቡም ከመቼው ግዜ በላይ እኛ ጠንካራ ሆነን እንደቆምን ለዓለም እያረጋገጥን እንገኛለን” ሲሉ ለስፑትኒክ አፍሪካ ተናግረዋል፡፡
የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትሩ አብዱልቃሲም ኢብራሂም ፎብማ በበኩላቸው፤ የኤግዚቢሽኑ ስፋት እና የተሳታፊዎች ብዛት ማሊ "ለአጋርነት ዝግጁ የሆነች ሀገር" መሆኗን ያረጋግጣል በማለት ለስፑትኒክ አፍሪካ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X