ሁለተኛው ሩሲያ-ሠር ኤምሲ-21 የሙከራ አውሮፕላን ከሳይቤሪያ ወደ ሞስኮ ያለማቋረጥ በረራውን አጠናቀቀ
10:58 14.11.2025 (የተሻሻለ: 11:14 14.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
ሁለተኛው ሩሲያ-ሠር ኤምሲ-21 የሙከራ አውሮፕላን ከሳይቤሪያ ወደ ሞስኮ ያለማቋረጥ በረራውን አጠናቀቀ
ከሳይቤሪያ ኢርኩትስክ ከተማ የተነሳው የመካከለኛ ርቀት አውሮፕላን ወደ ሞስኮ ዳርቻ ዙኮቭስኪ በረራ ማድረጉን የተባበሩት አውሮፕላን ኮርፖሬሽን አስታውቋል።
🟠 በሁለቱ መዳረሻዎች መካከል ያለው የቀጥታ መስመር ርቀት 4300 ኪሜ፣
🟠 6 ሰዓት ከ15 ደቂቃ የፈጀ በረራ፣
🟠 በ11 ሺ ሜትር ከፍታ እና በሰዓት 800 ኪሜ ፍጥነት የተከናወነ በረራ፡፡
"ረዥሙ በረራ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። አውሮፕላኑ ያለምንም እንከን በረራውን አከናውኗል፤ ሁሉም ሲስተሞችም ያለ ብልሽት ሠርተዋል" ሲሉ የበረራ ቡድኑ አዛዥ አንድሪ ቮሮፓይቭ ተናግረዋል።
የሙከራ አውሮፕላኑ አሁን በያኮቭሌቭ የበረራ ሙከራ ተቋም የዝግጅት ሂደት ውስጥ የሚያልፍ ሲሆን ከዚያም የገቢ ምርት መተካት መርሃ-ግብር አካል በመሆን የዕውቅና ማረጋገጫ ሙከራዎችን ይጀምራል ሲል ኮርፖሬሽኑ ገልጿል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

