በሩሲያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ላይ በኪዬቭ ድጋፍ የተቃጣ የግድያ ሴራን በድጋሚ እንዳከሸፈ የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አስታወቀ
10:24 14.11.2025 (የተሻሻለ: 10:44 14.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
በሩሲያ ከፍተኛ ባለሥልጣን ላይ በኪዬቭ ድጋፍ የተቃጣ የግድያ ሴራን በድጋሚ እንዳከሸፈ የሩሲያ የደህንነት አገልግሎት አስታወቀ
ከደህነነት አገልግሎቱ የተሰጡ ቁልፍ ዝርዝር ነጥቦች፡-
◾ ሴራው የተቀነባበረው ከምዕራባውያን የደህንነት ተቋማት ጋር በመሆን በዩክሬን የደህንነት አገልግሎት ነው፡፡
◾ የዘመዳቸውን ለቅሶ ለመድረስ በሞስኮ የመቃብር ስፍራን ሲጎበኙ የነበሩ ከፍተኛ የሩሲያ ባልሥልጣንን ዒላማ ያደረገ ነበር፡፡
◾ የመካከለኛው እስያ ስደተኛን ጨምሮ አራት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
◾ ከተያዙት መሳሪያዎች መካከል ሚስጥራዊ ኮድ የተሞላባቸው የመገናኛ መሳሪያዎች እና የርቀት መቆጣጠሪያ ያለው በሐሰተኛ የአበባ ማስቀመጫ ውስጥ የተደበቀ ካሜራ ይገኙበታል።
◾ መልዕክቶቹ በተጠርጣሪዎች እና በዩክሬን የስለላ ተቋማት መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት መኖሩን አረጋግጠዋል።
◾ ዩክሬን በሌላ የሩሲያ ክልል ተመሳሳይ ጥቃት ለመፈፀም እየተዘጋጀች ነው ሲል የደህንነት አገልግሎቱ አስጠንቅቋል፡፡
◾ በሩሲያ ሕግ መሠረት ከውጭ ኤጀንሲዎች ጋር በሚስጢር ትብብር ማድረግ ሕገ-ወጥ ሲሆን በእድሜ ልክ እስራት ያስቀጣል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X