የጋና ንጉስ አሻንቲ በመቶዎች የሚቆጠሩ የወርቅና የነሐስ ቅርሶች ከእንግሊዝ እና ከስዊዘርላንድ ተመለሱ
11:19 12.11.2025 (የተሻሻለ: 11:24 12.11.2025)

© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የጋና ንጉስ አሻንቲ በመቶዎች የሚቆጠሩ የወርቅና የነሐስ ቅርሶች ከእንግሊዝ እና ከስዊዘርላንድ ተመለሱ
የአሻንቲው ንጉሠ ኦሴይ ቱቱ ዳግማዊ በኩማሲ በሚገኘው የማንሂያ ቤተ-መንግሥት ሙዚየም በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት፣ ከውጭ አገር ተቋማት የተመለሱ ወሳን የሆኑ የንጉሣዊ ቅርሶችን ስብስብ ተቀብለዋል።
የተመለሱት ቅርሶች እንደ ንጉሣዊ አልባሳት፣ የስርዓት (የድግስ) ከበሮዎች እና የወርቅ መመዘኛዎች ያሉ 130 ያህል ቅርሶችን ያካትታሉ። አብዛኞቹ ቅርሶች ከዚህ ቀደም በዩናይትድ ኪንግደም እና በስዊዘርላንድ በተለይም በጄኔቫው ባርቢየር-ሙለር ሙዚየም ስር ነበሩ።
ይህ መመለስ ቀጣይነት ያለው ጥረት አካል ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. በ2024 ብቻ ከሚከተሉት ተቋማት 67 ሌሎች ቅርሶች ተመልሰው ነበር፡፡
🟠 ከብሪቲሽ ሙዚየም፣
🟠 ለንደን ከሚገኘው የቪክቶሪያ እና አልበርት ሙዚየም እና
🟠 ሎስ አንጀለስ ከሚገኘው የፎውለር ሙዚየም።
ይህ ክስተት የአፍሪካ አገራት በቅኝ ግዛት ዘመን የተዘረፈውን ባህላዊ ቅርስ ለማስመለስ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሲያደርጉት የቆየውን ትግል የሚያጎላ ሲሆን፤ ሂደቱም አንዳንድ የአውሮፓ ተቋማት አሁንም ሙሉ በሙሉ ለመመለስ መዘግየታቸውን ያመለክታል።
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X