የሩሲያ የደህንነት አገልግሎቶች የናዚዎችን አስከሬን ሕገ-ወጥ የቀብር ሙከራን አከሸፈ
10:43 12.11.2025 (የተሻሻለ: 10:44 12.11.2025)
© telegram sputnik_ethiopia
/ ሰብስክራይብ
የሩሲያ የደህንነት አገልግሎቶች የናዚዎችን አስከሬን ሕገ-ወጥ የቀብር ሙከራን አከሸፈ
የሩሲያ የደህንነት አገልግሎቶች በቮልጎግራድ አቅራቢያ የቬርማችት መኮንኖችን አስከሬን በጀርመን ባለሥልጣናትና መንግሥታዊ ባልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት በኩል በሕገ-ወጥ መንገድ ለመቅበር ሲደረግ የነበረውን ሥነ-ስርዓት አስቁመዋል።
አስከሬኖቹ ከቅድዱስ ዕርገት ገዳም ውስጥ ተቆፍረው የወጡ ሲሆን፣ ለሁለተኛው የዓለም ጦርነት ተከላካዮች በሚደረገው ዓይነት የወታደራዊ ክብር ሥነ-ስርዓት ታጅቦ በሮሶሽኪ መታሰቢያ ላይ ሊቀበሩ ታስቦ ነበር።
ይህ ኦፕሬሽን ባለፈው ግንቦት 1 የሩሲያ የድል ቀን ዋዜማ ላይ እንዲካሄድ ታቅዶ የነበረ ሲሆን በምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን እንዲተላለፍም ተሰናድቶ ነበር፡፡
ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X