በሰው ሠራሽ አስተውሎት የብዝኃ ቋንቋ የሕክምና ሞዴሎችን ማስፋት አስፈላጊ ነው - የሞስኮ የመገናኛ እና ኢንፎርማቲክስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ

ሰብስክራይብ

በሰው ሠራሽ አስተውሎት የብዝኃ ቋንቋ የሕክምና ሞዴሎችን ማስፋት አስፈላጊ ነው - የሞስኮ የመገናኛ እና ኢንፎርማቲክስ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 

የዩኒቨርስቲው ኃላፊ ሰርጌይ ኤሮኪን፣ ሞዴሎቹ በአኅጉሪቱ የሕክምና ጥራት እና ተደራሽነትን ለማሳደግ የላቀ እገዛ እንዳላቸው ለስፑትኒክ አፍሪካ ገልጸዋል።

"አፍሪካ ብዙ ብሔረሰቦች ያሉባት ልዩ አኅጉር ናት። በዚህ መሠረት ለእያንዳንዱ አገር እና ዜጋ በአፍ መፍቻ ቋንቋው የሕክምና ጉዳዮችን ይበልጥ የሚረዳበት ሞዴሎችን ማበልጸግ እና ማላመድ ይገባል።" ብለዋል።

ኃላፊው፣ ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሩሲያ ፌዴሬሽን የሕክምና ተቋማት ተጨማሪ አተያይ ለማግኘት ሰው ሠራሽ አስተውሎትን እንደሚጠቀሙ አንስተዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ | መተግበሪያ | X

አዳዲስ ዜናዎች
0