ኢትዮጵያና አልጄሪያ የንግድ ትስስራችውን ለማጠናከር ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያና አልጄሪያ የንግድ ትስስራችውን ለማጠናከር ተስማሙየንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ በአልጄሪያ የኢነርጂ፣ ማዕድንና ታዳሽ ኃይል ሚኒስትር መሐመድ አርካብ የተመራን ልዑክ ዛሬ ተቀብለው እንዳነጋገገሩ ገልፀዋል። "ከአልጄሪያ ጋርም የንግድ ትስስራችንን ለማጠናከር በምንችልባቸው አግባቦች ዙሪያ ገንቢ ውይይት አድርገናል፡፡ አልጄሪያ በኢነርጂ ልማትና አስተዳደር የዳበረ ልምድ ያላት ሲሆን በዚህ ረገድ  በሚኒስቴር መስሪያቤታችን ለምንሠራቸው ሥራዎች አጋዥ የሚሆኑ የቴክኒክና የስልጠና ልውውጦችን ለማድረግ ተስማምተናል፡፡ ልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያ ባካሄደችው ሪፎርምና በተገኙ ተጨባጭ ውጤቶች ያላቸውን አድናቆትም ገልጸዋል" ሲሉ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ተናግረዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0