የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነት ቢሻሻልም የጠበቀ ግን ሊሆን አይችሉም ሲሉ አሜሪካዊው ተንታኝ ተናገሩ

ሰብስክራይብ
የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነት ቢሻሻልም የጠበቀ ግን ሊሆን አይችሉም ሲሉ አሜሪካዊው ተንታኝ ተናገሩ "በአሜሪካ ጠብ አጫሪና የውጊያ የውጭ ፖሊሲ ምክንያት ዩናይትድ ስቴትስ ከአብዛኛው ዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አይኖራትም። በዚህም የአሜሪካና የሩሲያ ግንኙነት ይሻሻላል፤ ብዙም የጠበቀ ግን ላይሆን ይችላል። ብሪክስ እና የዩሬዥያ ክልላዊ ስብስብ ለአዲሱ የባለ ብዙዋልታ ዓለም ወሳኝ ናቸው" ሲሉ ታዋቂው አሜሪካዊ የኢኮኖሚ ምሑር እና የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር ለአርአይኤ ኖቮስቲ ገልፀዋል። የአሜሪካ እና ሩሲያ ግንኙነት እየተሻሻለ ቢሆንም ሩሲያ ከቻይና፣ ህንድ፣ ኢራን፣ ከአረብ ሀገራት፣ ከአፍሪካ እና ከሌሎች ጋር ያላት ግንኙነት ከአሜሪካ ጋር ከሚኖራት የበለጠ ቦታ እንደሚኖረው ምሑሩ ጠቁመዋል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካ ከሌለችበት የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል-ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) ለሩሲያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ስጋት አይደቅንም ሲሉ ቀደም ሲል ተናግረዋል። ፑቲን እና ትራምፕ ማክሰኞ ባካሄዱት የስልክ ውይይት በዩክሬን ጦርነት መፍትሄ ዙሪያ እንደተወያዩ እና መደበኛ ግንኙነት ለመጀመር የጋራ ፍላጎት እንዳላቸው ማመልከታቸውን ክሬምሊን ገልጿል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0