ሩሲያ የአፍሪካን የኃይል ክፍተት ለመሙላት ዝግጁ ነኝ አለች

ሰብስክራይብ
ሩሲያ የአፍሪካን የኃይል ክፍተት ለመሙላት ዝግጁ ነኝ አለች የሩሲያ ኢነርጂ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ዳይሬክተር ዲሚትሪ ፖዱዬቭ ሀገሪቱ የኢነርጂ ሀብቶችን ለማቅረብና ቴክኖሎጂዎች እና ልምዶችን ለማጋራት ፍቃደኛ ነች ብለዋል። የሩሲያ እገዛ በአዲስ የማምረቻ መሠረተ ልማት ዙሪያ አቅም መገንባት እና ነባር መሠረተ ልማቶችን ማዘመን ላይ እንደሚያተኩር ጠቁመዋል። "ሩሲያ፣ ህንድ እና አፍሪካ፡ ያለፈው ትምህርት እና የወደፊቱ ተስፋ" በሚል ርዕስ መጋቢት 10 በሞስኮ በተካሄደው ሲምፖዚየም ላይ ንግግር ያደረጉት ፖዱዬቭ፤ የሩሲያ ድርጅቶች የአፍሪካን የኃይል ፍላጎት ለማሟላት በቂ አቅም እንዳላቸው ገልፀዋል። የአፍሪካ ሀገራት በበኩላቸው በ2019 እና 2023 በተካሄዱት ሁለቱ የሩሲያ-አፍሪካ ጉባዔዎች፤ ከሩሲያ ጋር ለመተባበር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳየታቸውን ፖዱዬቭ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0