የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ሆና ማየት እንደሚፈልጉ ገለጹ

ሰብስክራይብ
የዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኢትዮጵያ የድርጅቱ አባል ሆና ማየት እንደሚፈልጉ ገለጹየንግድ እና ቀጠናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ ከዓለም ንግድ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኒኮዚ አዌላ ጋር ተወያይተዋል፡፡ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የዓለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ጥረት ያካሄደቻቸውን የሁለትዮሽ እና የባለ ብዙ ወገን ድርድሮች ለዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሯ ኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባል ሆና ማየት ትልቁ ውጥናቸው መሆኑንና የትኛውንም ዓይነት ድጋፍ ለማድረግ እንደማይቆጠቡ ማስታወቃቸውን ሚኒስትሩ በማሕበራዊ ትሥሥር ገፃቸው ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም ለአፍሪካ ቡድን እና ለአባል ሀገራት የኢትዮጵያን የአባልነት ድርድር እንዲደግፉ ይፋዊ ጥሪ እንደሚያስተላልፉ መግለፃቸውን ሚኒስትር ካሳሁን ጠቁመዋል።@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0