ደቡብ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ሰብስክራይብ
ደቡብ ሱዳን እና ሳዑዲ አረቢያ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር በሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሊድ ቢን አብዱልከሪም የተመራ የልዑካን ቡድንን በጁባ አግኝተዋል።የሳዑዲ አረቢያ ምክትል ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር እና የደቡብ ሱዳን ምክትል ሚኒስትር መንደይ ሰማያ ኩምባ ሁለቱ ሀገራት በንግድ፣ በኢንቨስትመንት እና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያላቸውን ቁርጠኝነት እና ትሥሥራቸው ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።ፕሬዝዳንት ኪር የልዑካን ቡድኑን ተቀብለው ሳዑዲ አረቢያ የደቡብ ሱዳን ቁልፍ የልማት አጋር እንደሆነች እውቅና የሰጡ ሲሆን፤ ሁለቱ ሀገራት ትብብራቸውን ለማስፋት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸውም አመላክተዋል፡፡በእንግሊዘኛ ያንብቡ@sputnik_ethiopia መተግበሪያ | X ላይ ይከተሉን
አዳዲስ ዜናዎች
0