ሶማሊያ እና ሶማሌላንድ የፍልስጤማውያንን ሠፈራ በተመለከተ ከአሜሪካ ወይም እስራኤል ምንም ዓይነት እቅድ አልደረሰንም ሲሉ አስተባበሉ

ሰብስክራይብ
ሶማሊያ እና ሶማሌላንድ የፍልስጤማውያንን ሠፈራ በተመለከተ ከአሜሪካ ወይም እስራኤል ምንም ዓይነት እቅድ አልደረሰንም ሲሉ አስተባበሉ የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ የፍልስጤም ሕዝብን በመሬቱ የመኖር መብት የሚነፈግ የትኛውንም እቅድ ሀገራቸው ሙሉ በሙሉ ውድቅ ታደርጋለች ማለታቸውን ምዕራባውያን መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል። የሶማሌላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲራህማን ዳሂር አዳን "ፍልስጤማውያንን በተመለከተ ከማንም ጋር ያደርግነው ውይይት የለም" ብለዋል። በአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የድህረ ጦርነት እቅድ መሠረት፤ የአሜሪካ እና እስራኤል ባለስልጣናት ከጋዛ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያንን ለማሥፈር ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ሶማሊላንድን እንዳናገሩ መዘገቡ የሚታወስ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0