ኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን 55ኛ ዓመት አከበሩ

ሰብስክራይብ
ኢትዮጵያ እና ቻይና የዲፕሎማሲ ግንኙነት የጀመሩበትን 55ኛ ዓመት አከበሩ ቀኑ "55 ዓመታት፦ ጠንካራ አጋርነት ለጋራ ብልጽግና በሚል መሪ ቃል" በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተከብሯል። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ኢትዮጵያና ቻይና ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ በጋራ መተማመን፣ መከባበር እና መተባበር ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መፍጠራቸውን በዚሁ ወቅት ተናግረዋል።የሕዝባዊት ሪፐብሊክ ቻይና የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ቼን ሺያኦዶንግ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው የቻይና አጋሮች አንዷ መሆኗን ጠቅሰው፤ ቻይና የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0