የሰርቢያ ፓርላማ የብሪክስ ትብብር ቡድንን አቋቋመ ቡድኑ በሰርቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ቩሊን እና በሶሻሊስቶች ንቅናቄ (ዲኤስ) ፓርቲ አነሳሽነት እንደተቋቋመ እና በምዝባ ሂደት ላይ እንደሆነ የዲያስፖራ እና ሰርቦች ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት ድራጋን ስታኖጄቪች ለስፑትኒክ ተናግረዋል። "የዲኤስ ምክትል ፕሬዝዳንት ቦጃን ቶርቢካ የቡድኑ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጠዋል። እኔ ምክትል ሆኛለሁ። ፓርቲያችን (የህዝብ ድምጽ) ይህንን ሙሉ በሙሉ ይደግፋል። ሂደቱ ከትናንት በስቲያ ለፓርላማ ቀርቧል” ሲሉ ስታኖጄቪች ተናግረዋል። ሆኖም ገዥው የሰርቢያ ተራማጅ ፓርቲ ተነሳሽነቱን የተቃወመው ሲሆን 18 የሕግ አውጭዎች ግን ደግፈውታል ያሉት ባለስልጣኑ፤ ቡድኑን የተመለከቱ መረጃዎች በቅርቡ በፓርላማው ድረ-ገጽ ላይ እንደሚለጠፉ ገልጸዋል። የብሪክስ ትብብር ቡድን ቻርተር እንደተዘጋጀ እና ፍላጎት ያላቸው ሀሉም ተወካዮች ማግኘት እንደሚችሉ ተናግረዋል። "ይህ ለወደፊት ጥሩ ውጤት የሚያመጣ አዎንታዊ ሁነት ነው ብዬ አምናለሁ" ሲሉ ስታኖጄቪች አክለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
የሰርቢያ ፓርላማ የብሪክስ ትብብር ቡድንን አቋቋመ
የሰርቢያ ፓርላማ የብሪክስ ትብብር ቡድንን አቋቋመ
Sputnik አፍሪካ
የሰርቢያ ፓርላማ የብሪክስ ትብብር ቡድንን አቋቋመ ቡድኑ በሰርቢያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ቩሊን እና በሶሻሊስቶች ንቅናቄ (ዲኤስ) ፓርቲ አነሳሽነት እንደተቋቋመ እና በምዝባ ሂደት ላይ እንደሆነ የዲያስፖራ እና ሰርቦች ኮሚቴ ሰብሳቢ... 09.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-09T19:09+0300
2025-03-09T19:09+0300
2025-03-09T19:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий