ገዢው የካናዳ ሊብራል ፓርቲ ዛሬ መሪውን ይመርጣል

ሰብስክራይብ
ገዢው የካናዳ ሊብራል ፓርቲ ዛሬ መሪውን ይመርጣል የቀድሞ የካናዳ ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ማርክ ካርኒ፣ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር ክሪስቲያ ፍሪላንድ፣ የቀድሞ ሕግ አውጪ ፍራንክ ቤይሊስ እና በታችኛው የካናዳ ፓርላማ የመንግሥት ተጠሪ የነበሩት ካሪና ጉልድ በምርጫው ላይ የተሳተፉት አራቱ እጩዎች ናቸው። በመላው ሀገሪቱ የተመዘገቡ የፓርቲ አባላት ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ድምጽ የሰጡ ሲሆን፤ ውጤቱ በሀገሪቱ ዋና ከተማ ኦታዋ ዛሬ በሚካሄድ ዝግጅት ይፋ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ካናዳን ከአስር ዓመታት በላይ ያስተዳደሩት ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ በጥር ወር መጀመሪያ ስልጣን የመልቀቅ ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸው ይታወሳል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክ  ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0