ኬኒያ ኢትዮጵያን ተጠቅማ ሰፊውን የሰሜን አፍሪካ ገበያ መድረስ ትችላለች ሲሉ የኬኒያ አምራቾች ማሕበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናገሩ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር ያላት ትስስር፤ የኬንያ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ሰፊው የሰሜን አፍሪካ እንዲያስገቡ እድል ይፈጥራል ሲሉ የኬኒያ አምራቾች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ቶቢያስ አላንዶ ተናገረዋል።ዋና ስራ አስፈፃሚው ቶቢያስ አላንዶ አዲስ አበባ ተካሂዶ በነበረው የኢትዮ-ኬኒያ የቢዝነስ ኮንፈረንስ ላይ ያሉት ነው። “ኬኒያ እና ኢትዮጵያ በዙሪያቸው ያሉ ሌሎች ሀገራትን ለመድረስ በጋራ መስራት ይችላሉ። ይህ ትብብር ሁለቱንም ሀገራት ይጠቅማል" ብለዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሃንስ ፋንታ በበኩላቸው ኢትዮጵያ እና ኬንያ በመከባበር፣ በወጥነት እና በመግባባት ላይ የተመሠረተ የቆየ እና ልዩ የዲፕሎማሲያዊ ግኑኝነት እንዳላቸው ተናግረዋል። "ከሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ አቅም አንፃር ህዝቦቻችን ተቀራርበው መሥራት የሚችሉባቸው ብዙ የንግድ እና የኢንቨስትመንት እድሎች አሉ" ብለዋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
ኬኒያ ኢትዮጵያን ተጠቅማ ሰፊውን የሰሜን አፍሪካ ገበያ መድረስ ትችላለች ሲሉ የኬኒያ አምራቾች ማሕበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናገሩ
ኬኒያ ኢትዮጵያን ተጠቅማ ሰፊውን የሰሜን አፍሪካ ገበያ መድረስ ትችላለች ሲሉ የኬኒያ አምራቾች ማሕበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
ኬኒያ ኢትዮጵያን ተጠቅማ ሰፊውን የሰሜን አፍሪካ ገበያ መድረስ ትችላለች ሲሉ የኬኒያ አምራቾች ማሕበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናገሩ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ጋር ያላት ትስስር፤ የኬንያ አምራቾች ምርታቸውን ወደ ሰፊው የሰሜን አፍሪካ... 06.03.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-03-06T08:19+0300
2025-03-06T08:19+0300
2025-03-06T09:14+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
ኬኒያ ኢትዮጵያን ተጠቅማ ሰፊውን የሰሜን አፍሪካ ገበያ መድረስ ትችላለች ሲሉ የኬኒያ አምራቾች ማሕበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ተናገሩ
08:19 06.03.2025 (የተሻሻለ: 09:14 06.03.2025)
ሰብስክራይብ