ዮርዳኖስ እና ግብፅ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተቀናቃኝ መንግሥት ለመመስረት የሚያደረገውን ሙከራ ተቃወሙ

ሰብስክራይብ
ዮርዳኖስ እና ግብፅ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ተቀናቃኝ መንግሥት ለመመስረት የሚያደረገውን ሙከራ ተቃወሙ "ትይዩ የሱዳን መንግሥት በመመሥረት፤ የሱዳንን ቀዉስ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት የሚያደናቅፉ እና የሱዳን ሪፐብሊክን አንድነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ ጥረቶችን የዮርዳኖስ መንግሥት ትቃወማለች" ሲል የዮርዳኖስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመግለጫ ገልጿል። ዮርዳኖስ የሱዳን ቀውስ የሀገሪቱ ደህንነት፣ መረጋጋት፣ ሉዓላዊነትና የዜጎችን ደህንነት በሚያስጠብቅ መልኩ ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት እንደምትድገፍ አረጋግጣለች። ይህ በእንዲህ እንዳለ የግብፅ ዲፕሎማሲ የፈጥኖ ደራሹ ኃይል እና አጋሮቻቸው የሚወስዱት እርምጃ በሱዳን ያለውን የሰብዓዊ ሁኔታ የበለጠ እያባባሰ ነው ሲል ገልጿል። "የግብፅ አረብ ሪፐብሊክ ሁሉም የሱዳን ኃይሎች የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም በሚያስከብር መልኩ ያለ ልዩነት እና የዉጭ ጣልቃ ገብነት አካታች የፖለቲካ ሂደት እንዲያስጀምሩ ጥሪ ታቀርባለች " ሲል የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0