በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ተልዕኮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሀገሪቱ የደቡብ ምዕራብ ክልል ለሚገኘው የቤይ ክልል ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ለገሱ

ሰብስክራይብ
በሶማሊያ የአፍሪካ ሕብረት ተልዕኮ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት በሀገሪቱ የደቡብ ምዕራብ ክልል ለሚገኘው የቤይ ክልል ሆስፒታል የህክምና ቁሳቁስ ለገሱበአፍሪካ ሕብረት የድጋፍና ማረጋጋት ተልዕኮ ውስጥ የተሰማሩ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት አንታይባዮቲኮችን፣ መርፌዎችን፣ ጓንቶችን፣ ማስኮችን፣ የተለያዩ የቁስል ማሰሪያዎችን እና መተንፈሻዎችን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ቅዳሜ እለት ለሆስፒታሉ ለግሰዋል።የአፍሪካ ሕብረት የሶማሊያ ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ ደረጃ ሁለት ሆስፒታል ኮማንደር ሌ/ኮሎኔል ተረፈ ዘመድኩን፤ ድጋፉን ለክልሉ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሰኢድ አህመድ አሊ አስረክበዋል። የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት የሲቪል-ወታደራዊ ትብብር ሀላፊነታቸውን፤ በባይዶዋ ደረጃ ሁለት ሆስፒታል ለነዋሪዎች ነፃ የህክምና አገልግሎት በመስጠት እንደተወጡም ተልዕኮው በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0