የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለብራዚል ኢንቨስተሮች እድል የፈጠረ ነው ተባለ

ሰብስክራይብ
የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ለብራዚል ኢንቨስተሮች እድል የፈጠረ ነው ተባለ ይህ የተገለጸው በብራዚል ዋና ከተማ ብራዚሊያ በተካሄደው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ ፎረም ላይ ነው። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ የብራዚል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያለውን ምቹ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ተጠቅመው መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ሀገር መሆኗ እና በአዲስ አበባ እና ሳኦ ፖሎ ከተሞች መካከል ዕለታዊ በረራ መኖሩ የብራዚል ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ ምቹ ዕድል የፈጥረ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በፎረሙ ላይ የተሳተፉ የብራዚል ኩባንያዎች፤ በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት ተሳትፎ በማድረግ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ነቱሪዝም ልውውጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማህበራዊ የትሥሥር ገፁ አመልክቷል። መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦   APK ፋይል ሊንክስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0