የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አሜሪካ ጥሬ እቃዎችን ከሀገራቸው በቀጥታ እንድትገዛ በማሳሰብ፤ ሩዋንዳ ዘርፋናለች ሲሉ ከሰሱ

ሰብስክራይብ
የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት አሜሪካ ጥሬ እቃዎችን ከሀገራቸው በቀጥታ እንድትገዛ በማሳሰብ፤ ሩዋንዳ ዘርፋናለች ሲሉ ከሰሱ ፌሊክስ ሺሴኬዲ የእነዚህ የተፈጥሮ ሀብቶች ትክክለኛ ባለቤት ሀገራቸው እንጂ ሩዋንዳ አይደለችም ያሉ ሲሆን፤ ሩዋንዳ ብጥብጥን ተገን በማድረግ ምዝበራ ፈፅማብናለች ሲሉ ከሰዋል።  የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ቲና ሳላማ ጥያቄው ከሩዋንዳ የማዕድን ግዢ ለሚፈፅሙ የአውሮፓ ሀገራት እና ሌሎች ገዥዎችም እንደቀረበ በመግለፅ፤ የግጭት ማዕድናትን ከሩዋንዳ መግዛት ችግር እንደሚፈጥርባቸው አስጠንቅቀዋል። የቃል አቀባይዋ አስተያየት ዩናይትድ ስቴትስ በምስራቅ ኮንጎ እየተካሄደ ባለው ግጭት ውስጥ እጃቸው አለበት ባለቻቸው የሩዋንዳ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ ከጣለች በኋላ የመጣ ነው።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0