የኒጀር የሽግግር መንግሥት በአምስት ዓመት እንዲራዘም ሃሳብ ቀረበ

ሰብስክራይብ
የኒጀር የሽግግር መንግሥት በአምስት ዓመት እንዲራዘም ሃሳብ ቀረበ በቅርቡ በተካሄደው የብሔራዊ ኮንፈረንስ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ፤ ኒጀር እ.አ.አ 2023 ተካሄዶ ሉዓላዊነቷ እና ነፃነቷ ላይ አደጋ ጥሎ የነበረው የመፈንቅለ መንግሥት የደቀነባትን አደጋ አጉልቶ አሳይቷል። የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የብሔራዊ ምክር ቤቱ የሀገሪቱን የግዛት አንድነት በማስጠበቅ፣ ብሔራዊ አንድነትን በማጎልበት እና የኒጀር ሕዝብን መሠረታዊ ጥቅሞች በማስጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት እውቅና ሰጥተዋል።  ፕሬዝዳንት አብዱራህማኔ ቺያኒ እና አመራራቸው የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማጠናከር እና ብሔራዊ ክብርን ለመመለስ ያሳያቱን ቁርጠኝነትም  አወድሰዋል። የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች የሽግግር ጊዜው በሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታ፣ በዝርዝር የማገገሚያ ሁኔታዎች እና በሳህል ሀገራት ኮንፌዴሬሽን አጀንዳ ላይ እንዲመሠረት ሀሳብ አቅርበዋል። ነባር የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲበተኑ እና አዲስ የፖለቲካ ቻርተር እንዲፀድቅም ሀሳብ አቅርበዋል። በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
አዳዲስ ዜናዎች
0