አፍሪካ "የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ምሰሶ ናት" ሲሉ በስፑትኒክ የኢትዮጵያ ማዕከል የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ የምዕራባውያን ሀገራት የራሳቸውን ዓይነት ዴሞክራሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመጫን ፍላጎታቸውን ለማስፈጸም አብዛኛውን ግዜ የሌሎች ሀገራትን ሉዓላዊነትና ወግ ይንቃሉ ሲሉ፤ ቫለንቲና ማትቪዬንኮ የስፑትኒክ የኤዲቶሪያል ማዕከል በኢትዮጵያ ከተከፈተ በኋላ ተናግረዋል። "ምዕራቡ ዓለም ሌሎችን ለፍላጎቱ የማስገዛትና የማፈን ፖሊሲን ይከተላል፣ ይህንንም ብሔራዊ ጥቅማቸውን ብቻ በማሳደድና ጨቋኝ በሆነ መንገድ ያደርጉታል" ሲሉ ከስፑትኒክ የዜና ወኪል የእናት ድርጅት ሮስያ ሴጎድኒያ ዋና ዳይሬክተር ዲሚትሪ ኪሴሌቭ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ተናግረዋል። ይህ አካሄድ ሀገራት ከራሳቸው ባህላዊና ታሪካዊ ሁኔታ ጋር የማይጣጣም የእድገት ሞዴል እንዲከተሉ ያስገድዳቸዋል። በአንፃሩ ሩሲያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የምታደርገው ትብብር ሉዓላዊነትን የሚያከብር እና የጋራ ልማትን የሚያበረታታ ነው። በሰፊ የተፈጥሮ ሀብቷ እና እያደገ በመጣው ኢኮኖሚዋ፤ አፍሪካ የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ቁልፍ ምሰሶ እየሆነች መምጣቷን ማትቪዬንኮ ጠቁመዋል። "ዓለም ወደ ባለ ብዙ ዋልታ መዋቅር እየሄደች ነው" ያሉት ማትቪዬንኮ "አፍሪካ በፍጥነት እያደገ በመጣው በዚህ ባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ቁልፍ ከሆኑ ምሰሶዎች አንዷ ትሆናለች፤ ነችም" ብለዋል።በእንግሊዘኛ ያንብቡ መተግበሪያውን አሁኑኑ ያውርዱ፦ APK ፋይል ሊንክ ስፑትኒክ ኢትዮጵያን ይወዳጁ @sputnik_ethiopia
https://amh.sputniknews.africa
አፍሪካ "የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ምሰሶ ናት" ሲሉ በስፑትኒክ የኢትዮጵያ ማዕከል የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
አፍሪካ "የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ምሰሶ ናት" ሲሉ በስፑትኒክ የኢትዮጵያ ማዕከል የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
Sputnik አፍሪካ
አፍሪካ "የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ምሰሶ ናት" ሲሉ በስፑትኒክ የኢትዮጵያ ማዕከል የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ የምዕራባውያን ሀገራት የራሳቸውን ዓይነት ዴሞክራሲ በዓለም አቀፍ ደረጃ በመጫን... 20.02.2025, Sputnik አፍሪካ
2025-02-20T11:18+0300
2025-02-20T11:18+0300
2025-02-20T11:44+0300
https://cdn.amh-img.sputnikglobe.com/i/logo/logo-social.png
африка общий
2025
ዜናዎች
am_ET
Sputnik አፍሪካ
африка общий
африка общий
አፍሪካ "የባለ ብዙ ዋልታ ዓለም ምሰሶ ናት" ሲሉ በስፑትኒክ የኢትዮጵያ ማዕከል የመጀመሪያውን ቃለ መጠይቅ ያደረጉት የሩሲያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ተናገሩ
11:18 20.02.2025 (የተሻሻለ: 11:44 20.02.2025)
ሰብስክራይብ